የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም ወደ "ፋይዳቨርስ" (FaydaVerse) የመንግስት ልማት ድርጅትነት ሲቀየር እኔም በዚህ ታሪካዊ ዝግጅት ላይ ተጋብዤ ታድሜ ነበር! በዝግጅቱ ላይ ያየኋቸው እና ህዝቡን በቀጥታ የሚጠቅሙ 2 ዋና ዋና አዳዲስ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በአጭሩ ላካፍላችሁ፦ 1. አዲሱ "ፋይዳ ፓስ" (Digital Wallet) App፦ ከዚህ በኋላ መታወቂያ፣ የትምህርት ማስረጃ እና ሌሎች ሰነዶችን በወረቀት ይዞ መንከራተት ሊቀር ነው። አዲሱ መተግበሪያ ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶቻችንን በስልካችን ላይ በአንድ ደህንነቱ በተጠበቀ Digital Wallet ውስጥ እንድናስቀምጥ ያስችለናል። 2. የ Face ID እና አሻራ ማረጋገጫ፦ ከዚህ በፊት ማንነትን የምናረጋግጠው በስልክ በሚላክ የፅሁፍ መልዕክት (OTP) ብቻ ነበር። አሁን ግን አሰራሩ ዘምኖ የሰዎችን የፊት ገጽታ (Face ID) እና የጣት አሻራ በመጠቀም ማንነትን በ Digital መንገድ በቀላሉ ማረጋገጥ ተችሏል። በአጠቃላይ እስካሁን ከ 50 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በዲጂታል መታወቂያው የተመዘገቡ ሲሆን፣ የእኛ ሀገር ቴክኖሎጂ አድጎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የመሰረተ-ልማት ድጋፍ መስጠት መጀመሩን ስሰማ በጣም አስደስቶኛል። 👇 በዝግጅቱ ላይ ካየሁት ነገር፣ ሀገራችን በ Digital ቴክኖሎጂ እያደረገች ያለው ጉዞ እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው። እናንተስ የፋይዳ መታወቂያ አውጥታችኋል? ሀሳባችሁን Comment ላይ ፃፉልኝ!
#fayda #faydaverse #nationalid #fyadatech